ስለ የምድር ጨው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የምድር ጨው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ካጣ፣ እንደ ገና ጨው እንዴት መሆን ይችላል? ወደ ውጭ ተጥሎ በእግር ከመረገጥ በቀር ፈጽሞ ለምንም አይጠቅምም።
መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩና በሰማይ ያለ አባታችሁን እንዲያከብሩት መብራታችሁ እንዲሁ በሰዎች ፊት ይብራ።
ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።
ጨው መልካም ነው፤ የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ግን ምን ታደርጉታላችሁ? በእያንዳንዳችሁ ሕይወት የጨውነት ጣዕም ይኑርባችሁ! እርስ በርሳችሁም በሰላም ኑሩ፡፡
ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።
ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።
ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጣዕም ካጣ እንዴት ተመልሶ እንደ ገና የጨውነት ጣዕም ሊኖረው ይችላል? ለመሬትም ሆነ ለማዳበሪያነት የማይጠቅም በመሆኑ ወደ ውጪ ይጣላል፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!"
መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።
ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል አኗኗራችሁ መልካም መሆን አለበት።
በነገር ሁሉ ራስህን የመልካም ሥራ ምሳሌ አድርገህ ተገኝ፤ በትምህርትም ንጽህናን፣ ጨዋነት፣ የማይነቀፍ ጤናማ ቃላት ይኑርህ። ስለ እኛ የሚናገረው ምንም ክፉ ነገር እንዳይኖር። የማይነቀፍ ስህተት የሌለበትን፣ ነገር ግን ሊቃወም የሚሞክረውን የሚያሳፍር ቃላትን ተናገር።
ሰዎች መብራት አብርተው ቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ በቅርጫት ሥር አያስቀምጡትም።
ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? ያ ሰው ከጥበብ በሚገኝ ትሕትና በሥራው መልካም ሕይወትን ያሳይ።
ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
ስለዚህ ሠላም የሚገኝበትንና እርስበእርሳችን የምንተናነጽባቸውን ነገሮች እንፈልግ።