ስለ ተወዳጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ተወዳጅ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ቆላስይስ 3:12
ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
02 1ኛ ዬሐንስ 3:1
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።
03 ሮሜ 1:7
ይህ መልዕክት የተጻፈው በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱስ ሕዝብ ለመሆን ለተጠራችሁ በሮም ላላችሁት ሁሉ ነው። ከእግዚአብሔር ከአባታችንና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
04 ኤፌሶን 1:6
ይህ ሁሉ የተፈጸመው በሚወደው ልጁ እንዲያው በነጻ ስለ ተሰጠን ክቡር ጸጋው እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ ነው።
ወደ ግብዣው አዳራሽ አመጣኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ሰንደቁ ፍቅር ነው። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
06 ኤርሚያስ 31:3
እግዚአብሔር በኃላፊው ጊዜ ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፣ "እስራኤል ሆይ፣ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ። ስለዚህ በኪዳን ታማኝነት ወደራሴ ሳብሁሽ።
ሙሴ ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው በትክሻዎቹ መካከል ያርፋል።