ስለ የሰማይ ዜጎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የሰማይ ዜጎች የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ነገር ግን የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠብቅ የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን።
ስለዚህ እናንተ አሕዛብ ከቅዱሳንና ከእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አባላት ጋር የአንድ አገር ዜጎች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም።
በዚህ ምድር ምንም ዓይነት ዘላቂ ከተማ የለንም። ነገር ግን የምትመጣውን ከተማ እንጠብቃለን።
እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ። በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
ወዳጆች ሆይ፤ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍሳችሁን ከሚዋጉ ከኅጢኣት ምኞቶች እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።
አሁን ግን የሚፈልጉት የተሻለውን ሰማያዊ አገር ነው። ስለዚህም፣ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አያፍርም።
ምክንያቱም ሞታችኋል፤ ሕይወታችሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ ሰውሮታልና።
ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ እንኳ በሰማይ በሰው እጅ ያልተሰራ ዘላለማዊ ቤት በእግዚአብሔር እንደተሰራልን እናውቃለን።
በአባቴ ቤት ብዙ የመኖሪያ ስፍራ አለ፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ፣ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ ብዬ አልነግራችሁም ነበር። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ ዳግመኛ እመጣለሁ፣ ወደ ራሴም እወስዳችኋለሁ።`
ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።
እነዚህ ሁሉ የተሰጧቸውን ተስፋዎች ሳይጨብጡ እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ። ይልቁንም እነዚህን ተስፋዎች ከሩቅ አይተው ስለተቀበሏቸው በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውን ተገነዘቡ።
እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጠርቶ ሽልማቴን ለማግኘት በፊት ወዳለው ግብ እሮጣለሁ።
ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡
አሁን ግን፣ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደሆነችው ወደ ጽዮን ተራራ፣ አእላፋት መላእክት በደስታ ወደሚያመልኩባት ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መጥታችኋል፤