ስለ ነጻ መውጣት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ነጻ መውጣት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ስለዚህ ልጁ ነጻ ካወጣችሁ፣ በርግጥ ነጻ ትወጣላችሁ።
ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።
ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል።
እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።
ጌታም መንፈስ ነው፤የጌታም መንፈስ ባለበት ነፃነት አለ።
ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።
“ለድሆች የምሥራቹን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለምርኮኞች ነፃነትን፣ ለዕውሮች ብርሃናቸው እንደሚመለስላቸው ፣ የተጨቆኑትም መፈታትን እንደሚያገኙ
ከኃጢአት ነጻ ተደርጋችኋል፥የጽድቅም አገልጋዮች ሆናችኋል።
አሁን ግን ከኃጢአት ነጻ ስለተደረጋችሁና ለእግዚአብሔር ባሪያዎች ስለሆናችሁ ለመቀደስ ፍሬ ታፈራላችሁ። ውጤቱም የዘላለም ሕይወት ነው።
በተጨነቅሁ ጊዜ ያህዌን ጠራሁት እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ፡፡
አንድ ሰው በጌታ ባሪያ ሆኖ የተጠራ የጌታ ነፃ ሰው ነው፤ እንደዚሁም ነፃ ሆኖ ለእምነት የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው።