ስለ በመንፈስ መጸለይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በመንፈስ መጸለይ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ይሁዳ 1:20

እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ።

02 ሮሜ 8:26

እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በድካማችን ውስጥ ያግዘናል። እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ስለማናውቅ መንፈስ ቅዱስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይቻል መቃተት ስለ እኛ ይማልድልናል።

03 ኤፌሶን 6:18

ዓይነት ጸሎትና ልመና ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይና መልሱን ከእርሱ በመጠበቅ፥ ለቅዱሳንም ልመና በማቅረብ ትጉ።

04 1ኛ ቆሮንቶስ 14:15

ታዲያ ምን ላድርግ? በመንፈሴም እጸልያልሁ፣በአእምሮዬም እጸልያለሁ። በመንፈሴ እዘምራለሁ፣በአእምሮዬም እዘምራለሁ።

05 ገላቲያ 4:6

ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።

06 ሮሜ 8:27

መንፈስ ቅዱስ ስለ አማኞች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለሚማልድ ልብን የሚመረምረው እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ሃሳብ ያውቃል።

07 1ኛ ቆሮንቶስ 14:14

በልሳን በምጸልይበት ጊዜ መንፈሴ ይጸልያል፣አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።

08 ዮሐንስ 4:23-24

ይሁን እንጂ፣ በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ አብ እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋልና። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።»

09 ዘካርያስ 12:10

በዚያ ቀን በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ ወጉኝ ወደ እኔ ይመለክታሉ፤ እነርሱም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ሰው ያለቅሱልኛል፤ ለበኩር ልጁ ሞት እንደሚያለቅስ ሰው ምርር ብለው ያለቅሳሉ።

ጸሎት ሲጨርሱ፣ ተሰብስበውበት የነበረው ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃልም በድፍረት ተናገሩ።

11 ፊልጵስዩስ 3:3

እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፤ በሥጋም የማንታመን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንታመን የተገረዝን ነን።

12 1ኛ ቆሮንቶስ 14:16

እንደዚያ ካልሆነ ግን እግዚአብሔርን በመንፈሳችሁ ብታመሰግኑና ሌላው ሰው በምታመሰግኑበት ሰዓት ምን እያላችሁ እንደሆነ ካላወቀ እንዴት "አሜን" ይላል?

13 ሮሜ 8:15

ተመልሳችሁ እንድትፈሩ የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም። ይልቅ የተቀበላችሁት "አባ፥አባት" ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ነው።

14 ገላቲያ 5:25

በመንፈስ የምንኖር ከሆነ በመንፈስ እንመላለስ።

15 ይሁዳ 1:20-21

እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ። በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ፤የዘላለም ሕይወትም ታገኙ ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ፈልጉ።

ተዛማጅ ርዕሶች