ስለ ኃጢአትን ማሸነፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ኃጢአትን ማሸነፍ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 6:14

ኃጢአት እንዲገዛችሁ አትፍቀዱለት። ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።

02 1ኛ ቆሮንቶስ 10:13

በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው በላይ የሆነ ፈተና አልደረሰባችሁም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አያደርግም። ይልቁን ፈተናውን መወጣት እንድትችሉ ከፈተናው ጋር ማምለጫ መንገዱንም ያዘጋጅላችኋል።

03 1ኛ ዬሐንስ 1:9

ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡

04 ሮሜ 8:13

እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ መሞታችሁ አይቀርም፥የሥጋን ሥራ በመንፈስ ቅዱስ ብትገድሉ ግን በሕይወት ትኖራላችሁ።

05 ያዕቆብ 1:14-15

እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲታለልና ሲሳብ ነው። ክፉ ምኞት ከተፀነሰ በኋላ ኀጢአት ይወለዳል፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞት ይወለዳል።

06 1ኛ ቆሮንቶስ 15:57

ነገር ግን በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል የሚሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

ተዛማጅ ርዕሶች