ስለ የእግዚአብሔር አገዛዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእግዚአብሔር አገዛዝ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ያህዌ ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች፡፡

እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ነግሦአል እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፡፡

03 ዳንኤል 4:35

የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማይ ሰራዊትና በምድር ሕዝቦች መካከል የወደደውን ያደርጋል። የሚያስቆመው ወይም የሚከራከረው የለም። “ለምን እንዲህ አደረግህ?” የሚለውም የለም።

04 1ኛ ዜና 29:11-12

እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ ለአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኅይል ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሄር ሆይ፤ መንግሥትህም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ። ባለጠግነት ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም በርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኅይል በእጅህ ነው።

መንግሥት የያህዌ ነውና ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው፡፡

አምላካችን በሰማይ ነው እርሱ ደስ የሚለውን አደረገ፡፡

07 ዳንኤል 4:34

ጊዜው ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዐይኖቼን ወደ ሰማይ አነሣሁ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ። “ልዑልንም ባረክሁት ለዘላለም የሚኖረውን እርሱን አመሰገንሁት አከበርሁት። እርሱ ለዘላለም ይነግሣልና መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ዘመን ነው።

በሕዝቦች መካከል፣ «እግዚአብሔር ነገሠ» በሉ፤ ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም፡፡ እርሱ ሕዝቦች ላይ በጽድቅ ይፈርዳል፡፡

09 ኢሳይያስ 40:15

ተመልከቱ፣ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ ተመልከቱ፣ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።

መንግሥትህ የዘላለም መግሥት ነው ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል፡፡

11 ኤፌሶን 1:11

ሁሉንም ነገር እንደ ገዛ ፈቃዱ በሚያደርገው ዕቅድ መሠረት በክርስቶስ ተመረጥን፤ አስቀድሞም ተወሰንን

ተዛማጅ ርዕሶች