ስለ ዕቅዶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ዕቅዶቹ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤርሚያስ 29:11

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ ራሴ አውቃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የጥፋት አይደለም።

02 ምሳሌ 19:21

በሰው ልብ ብዙ እቅዶች አሉ፣ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡

03 ኢሳይያስ 55:8-9

አሳቤ እንደ አሳባችሁ፣ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ፣ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

04 ሮሜ 8:28

እግዚአብሔርን ለሚወዱት፥ በዓላማው ለተጠሩት ለእነርሱ ሁሉን ነገር አጣጥሞ ለመልካም እንደሚሠራላቸው እናውቃለን።

ያህዌ እስከ መጨረሻ ከእኔ ጋር ነህ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ለዘላለም ነው፡፡ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል፡፡

የያህዌ ዕቅድ ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም ሐሳቡም ለትውልድ ሁሉ ነው፡፡

07 ኢሳይያስ 14:24

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፣ "እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፣ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።

08 ምሳሌ 16:9

ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፣ እግዚአብሔር ግን እርምጃውን ያቀናለታል፡፡

09 ኤፌሶን 2:10

ምክንያቱም እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት እንድንፈጽመው ያዘጋጀውን መልካም ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።

10 ኢሳይያስ 46:10

በመጀመሪያ መጨረሻውን፣ ከጥንትም ያልተደረገውን ሳይሆን በፊት እነግራለሁ፤ "ምክሬ ትጸናለች፣ ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ፤" እላለሁ።

ተዛማጅ ርዕሶች