ስለ ሸክላ ሠሪውና ጭቃው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሸክላ ሠሪውና ጭቃው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
አሁን ግን፣ አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፣ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።
"የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? ይላል እግዚአብሔር። ተመልከቱ! ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፣ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ ውስጥ አላችሁ።
በአንጻሩ ለእግዚአሔር መልስ የምትስጥ አንተ ማን ነህ? የሸክላ ጭቃ ቅርጽ ያወጣለትን ሰው ለምን እንደዚህ አድርገህ ሰራኽኝ ሊለው ይችላልን? ። ሸክላ ሰሪው ከዚያው ጭቃ አንዱን ለየት ባለ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውል ዕቃ ሌላውን ደግሞ በየቀኑ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ አድርጎ ሊሰራው በሸክላ ጭቃው ላይ ሥልጣን የለውም እንዴ?
ነገሮችን ገለባብጣችኋል! የተሠራው ነገር የሠራውን "አልሠራኝም፣" ይለው ዘንድ ሸክላ ሠሪው እንደ ጭቃው ሊቆጠር ይገባልን? ወይስ የተበጀው ነገር ያበጀውን "አታስተውልም" ይለዋልን?
ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ይህን በሚገባ ታውቃለች፡፡
እጆቸህ አበጃጁኝ አሳምረህም ሠራኸኝ፤ መልሰህ ግን እያታጠፋኸኝ እኮ ነው። እለምንሃለሁ፤ እንደ ሸክላ አበጃጅተህ እንደ ሰራኸኝ አስብ፤ እንደገናስ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው! ጭቃ የሚሠራውን፣ 'ምን ትሠራለህ?' ወይስ 'ሥራህ - እጅ የለውም' ይላልን?
ያህዌ አምላክ መሆኑን ዕወቁ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፡፡ እኛ ሕዝቡ የመሰማሪያውም በጐች ነን፡፡
እናንተ ተላላና ጥበብ የጎደላችሁ ሕዝብ፤ለእግዚአብሔር የምትመልሱለት በዚህ መንገድ ነውን? አባታችሁና ፈጣሪያችሁ የሠራችሁና ያበጃችሁእርሱ አይደለምን?
እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ተመልከት፥ በእግዚአብሔር ፊት አንተ እንደሆንከው እንዲሁም እኔም ነኝ፤ እኔም ደግሞ ከጭቃ ተሠርቻለሁ።
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፣ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።