ስለ ጥበብን አግኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጥበብን አግኝ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ምሳሌ 4:7
ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡
02 ምሳሌ 3:13-14
ጥበብን የሚያገኛት ሰው ደስተኛ ነው፣ እውቀትንም ያገኛል፡፡ ከጥበብ የምታገኘው ጥቅም ብር ከሚሰጥህ ትርፍ ይልቅ እጅግ ይበልጣል፣ የጥበብ ትርፍ ከወርቅም ይበልጣል፡፡
03 ምሳሌ 16:16
ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት ምንኛ ይበልጣል፡፡ ከብርም ይልቅ ማስተዋል ይመረጣል፡፡
04 ምሳሌ 8:11
እኔ ጥበብ፣ ከከበረ ዕንቁ እበልጣለሁና፤ ከምትመኙት ነገር በሙሉ ከእኔ ጋር የሚስተካከል የለም፡፡
05 ምሳሌ 23:23
እውነትን የራስህ አድርጋት፣ አትሽጣትም፤ ጥበብን፣ ስርዓትንና ማስተዋልንም ገንዘብህ አድርግ፡፡
06 ምሳሌ 2:1-5
ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ብትቀበልና ትእዛዛቴን በአንተ ዘንድ ብታኖር፣ ጥበብን ብታደምጥና ልብህን ወደ እውቀት ብትመልስ፡፡ እውቀትን ለማግኘት ብትጣራና ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስተዋል ብትጮህ፣ ብርን አጥብቀህ እንደምትፈልግ እርስዋንም ብትፈልጋት፣ የተሰወረ ሃብትን እንደምትፈልግ እንደዚሁ ማስተዋልን ብትሻት፣ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ፡፡
07 ምሳሌ 19:8
ጥበብን የሚያገኝ ሕይወቱን ይወዳል፤ ማስተዋልንም ገንዘቡ ያደረገ መልካም ነገር ያገኛል፡፡