ስለ በተወደደው ልጅ ተቀባይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በተወደደው ልጅ ተቀባይነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤፌሶን 1:6

ይህ ሁሉ የተፈጸመው በሚወደው ልጁ እንዲያው በነጻ ስለ ተሰጠን ክቡር ጸጋው እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ ነው።

02 ሮሜ 8:1

ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።

03 ቆላስይስ 1:21-22

እናንተም ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ነበር፤ በአሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶች ነበራችሁ። አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፤ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ በልጁ ሞት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። ይህም በእርሱ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ

04 ሮሜ 15:7

ልክ ክርስቶስ እንደተቀበላችሁ ለእግዚአብሔር ክብር እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ።

05 ዮሐንስ 6:37

አባቴ የሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ እኔም አባቴ የሰጠኝን ከቶ ወደ ውጭ አላባርርም፡፡

06 ገላቲያ 2:20

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

07 2ኛ ቆሮንቶስ 5:21

እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።

08 1ኛ ዬሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።

09 ገላቲያ 3:26

ምክንያቱም ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።

10 ሮሜ 8:15-16

ተመልሳችሁ እንድትፈሩ የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም። ይልቅ የተቀበላችሁት "አባ፥አባት" ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።

11 ዮሐንስ 1:12

ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡

12 ኤፌሶን 2:13

ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁት በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ ተደርጋችኋል።

13 ሮሜ 5:8

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች እያለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያረጋግጣል።

ተዛማጅ ርዕሶች