ስለ ትንሣኤና ሕይወት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ትንሣኤና ሕይወት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዮሐንስ 11:25
ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡
02 ዮሐንስ 11:26
በእኔ የሚኖርና የሚያምንብኝ ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?” አላት፡፡
03 ዮሐንስ 5:24
እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።
04 ዮሐንስ 6:40
የአባቴ ፈቃድ፣ ወልድን አይቶ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፡፡ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡››
በአዳም ሁሉም እንደሞቱ፣ሁሉም ደግሞ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ።