ስለ እግዚአብሔር ሰላማችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እግዚአብሔር ሰላማችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ስለዚህ ጌዴዎን በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፡፡ ስሙንም፣ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በምትሆነው በዖፍራ አለ፡፡
ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
በእምነት ስለ ጸደቅን በጌታችን በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።
በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
“ያህዌ ይባርችሁ ይጠብቃችሁ፡፡ ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡ ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’”
የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
አይሁድንና አሕዛብን ሁለቱን አንድ ሕዝብ ያደረገ እርሱ ሰላማችን ነውና ፤ በሥጋውም እርስ በርስ የለያየንን የጥል ግድግዳ አፈረሰ።
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።