ስለ ከታናናሾቹ አንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከታናናሾቹ አንዱ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’
ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤ ተራቊቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ' ይላቸዋል።
ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ ለሰራውም ቸርነት መልሶ ይከፍለዋል፡፡
እንግዶችን መቀበል አትርሱ፣ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋል።
እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ታናናሾች ለአንዱ፣ ደቀ መዝሙሬ ስለ ሆነ፣ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ማንም፣ በምንም ዐይነት ዋጋውን አያጣም፡፡
እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ አለማድረጋችሁ ለእኔ አለማድረጋችሁ ነው’ ይላቸዋል።
እንደዚህ ያለውን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፡፡
እውነት እላችኋለሁ የክርስቶስ በመሆናችሁ ምክንያት አንድ ብርጭቆ ውሃ እንድትጠጡ የሚሰጣችሁ ዋጋውን አያጣም፡፡
"እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል። እኔን የሚቀበል ከሆነ ደግሞ የላከኝን ይቀበላል። ስለሆነም፣ በመካከላችሁ ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና።”
ከዚያም ጻድቃን እንዲህ ብለው ይመልሱለታል፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ያገኘንህና ያበላንህ ወይስ ተጠምተህ ያጠጣንህ መቼ ነው? 38 እንግዳ ሆነህ ያየንህና ያስተናገድንህ መቼ ነው? ወይም ተራቊተህ ያለበስንህ መቼ ነው? ታምመህ የተንከባከብንህ ወይስ ታስረህ የጠየቅንህ መቼ ነው?’
ስለዚህም ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ።
አንድ ወንድም ወይም እኅት ልብስና የዕለት ምግብ ባይኖራቸው ከእናንተ አንዱ፣ “በሰላም ሂዱ፤ አይብረዳችሁ፤ በደንብ ጥገቡ” ቢላቸው፤ ለአካል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ግን ባትሰጧቸው፣ ምን ይጠቅማል?
ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ንብረት ያለውና፣ወንድሙም የሚያስፈልገውን አውቆ፣ባይራራለት፣ እንዴት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ይኖራል?
ከእነዚህ ከታናናሾች ማንኛውንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉና፡፡ 11 (2) ብዙ ምንጮች፣ አንዳንድ የጥንት የሆኑ ቊ. 11ን ያስገባሉ፡፡