ስለ በቂ ጸጋ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በቂ ጸጋ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።
ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በችግር፣ በስደት ፣ በጭንቀትም እርካታ ይሰማኛል በምደክምበት ጊዜ ሁሉ ብርቱ ነኝና።
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
ሥጋዬና ልቤ ደከሙ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም የልቤ ብርታትና አለኝታ ነው፡፡
ከእኛ የሆነ ብለን ልናስበው የምንችል አንዳች ችሎታ የለንም፤ነገር ግን ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው።
በዘመንህና ደህንነትህ ሁሉ የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሁን፤ ኃይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።
ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።
አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡