ስለ ጸጋ በጸጋ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጸጋ በጸጋ ላይ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀበልን፤
ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡
ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ በኩል መጣ፡፡
ነገር ግን ሕግ ከጎን በመግባቱ መተላለፍ በዛ። ይሁን እንጂ ኃጢአት በበዛበት በዚያ ጸጋ ይበልጡኑ በዛ።
እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።
እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው።
እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።
ይህንንም ያደረገው፥በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠውን የጸጋው ባለጠግነት ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ያሳይ ዘንድ ነው።
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ ፣ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለማዊ ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል ፤ ያበረታችኋልም።
ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የሚችለው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል፡፡