ስለ ስጦታን ማቀጣጠል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ስጦታን ማቀጣጠል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2 ጢሞቴዎስ 1:6

እግዚአብሔር የሰጠህን በአንተ ያለውን ስጦታ እንድታነሣሣ ስእጆቼን በመጫኔ አሳስብሃለሁ፡፡

02 2 ጢሞቴዎስ 1:7

እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡

03 1 ጢሞቴዎስ 4:14

በትንቢት ከሽማግሌዎች የእጅ መጫን ጋር ለአንተ የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል፡፡

04 1ኛ ጴጥሮስ 4:10

እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤

05 ሮሜ 12:6

በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው።

06 1 ጢሞቴዎስ 4:15

ለእነዚሀ ነገሮች ተጠንቀቅ፣ በእነርሱም ጽና፣ ይህን በማድረግህ ማደግህ በሁሉም ዘንድ ይገለጻል፡፡

07 2 ጢሞቴዎስ 4:5

አንተ ግን፣ በነገር ሁሉ የነቃህ ሁን፣ መከራን ተቀበል፣ የወንጌላዊነትን ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህንም ፈጽም፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች