ስለ ራስን መግዛት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ራስን መግዛት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ገላቲያ 5:23

የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።

02 ምሳሌ 25:28

ራሱን መግዛት የማይችል ሰው እንደፈረሰችና ቅጥር እንደሌላት ከተማ ነው፡፡

03 1ኛ ቆሮንቶስ 9:25

ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።

04 ቲቶ 2:12

ይህም ፀጋ ሃጢዓተኝነትና ዓለማዊ ምኞትን እንድንክድና፣ በአሁኑ ዘመን በጥንቃቄ፣ በጽድቅና፣ እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር ያስለምደናል

05 2ኛ ጴጥሮስ 1:6

በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፤

06 ምሳሌ 16:32

ጦረኛ ከመሆን ይልቅ ትዕግስተኛ መሆን ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚቆጣጠር ይልቅ ይበረታል፡፡

07 2 ጢሞቴዎስ 1:7

እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡

08 1ኛ ቆሮንቶስ 9:27

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ከውድድሩ ውጭ እንዳልሆን ሥጋዬን በመቆጣጠር አስገዛዋለሁ።

09 ያዕቆብ 1:19

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን!

10 ገላቲያ 5:24

የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ስሜቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል።

11 1ኛ ጴጥሮስ 5:8

ጠንቃቆች ሁኑ፤ ንቁም፤ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።

12 ምሳሌ 29:11

ሞኝ ቁጣውን ሁሉ ይገልጣል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ይቆጣጠራል፣ ራሱንም ያረጋጋል፡፡

13 1 ተሰሎንቄ 5:6

እንግዲያውስ ሌሎች እንደሚያደርጉት አናንቀላፋ፣ ነገር ግን እንንቃ በመጠንም እንኑር።

14 ሮሜ 13:14

ይልቁኑ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ለሥጋችሁና ለክፉ ምኞቱም ዕድል አትስጡ።

ተዛማጅ ርዕሶች