ስለ የመንፈስ ስጦታዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የመንፈስ ስጦታዎች የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ደግሞም ለእያንዳንዱ መንፍስ ቅዱስን መግለጥ የተሰጠው ለሁሉም ጥቅም ሲባል ነው።
ነገር ግን፣ለእያንዳንዳቸው እንደወደደ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በመስጠት በእነዚህ ሁሉ የሚሠራው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው።
ለአንዱ የጥበብ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣል፣ለሌላው ደግሞ የእውቀት ቃል በዚያው መንፈስ ይሰጣል። ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፣ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የፈውስ ስጦታ ይሰጠዋል። ለሌላው ደግሞ የኃይል ሥራዎች፣ለሌላው ትንቢት መናገር። ለሌላው ደግሞ መናፍስትን መለየት፣ለሌላው በልዩ ልዩ ልሳኖች መናገር፣እና ለሌላው ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ይሰጠዋል።
ወንጌል ሰባኪዎችን፥እረኞችን እና አስተማሪዎችን ስጦታ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስ ራሱ ነው። ያደረገው የክርስቶስን አካል ለማነጽና ለአገልግሎት ሥራ ቅዱሳንን ለማስታጠቅ ነው።
እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ሐዋርያትን፣ሁለተኛ ነቢያትን፣ሦስተኛ አስተማሪዎችን፣ከዚያም ተአምራት ማድረግን፣በመቀጠል የፈውስ ስጦታዎችን፣እርዳታ የሚያደርጉትን፣ የአስተዳደር ሥራ የሚሠሩትን፣ እና ልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችን የሚናገሩትን ሰጥቷል።
እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤
በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው። የአንዱ ስጦታ ደግሞ ቸርነት ማድረግ ከሆነ ቸርነት ያድርግ። የማስተማር ስጦታ ያለው ያስተምር። የማጽናናት ስጦታ ያለው ያጽናና፤ የመስጠት ስጦታ ያለው በልግስና ያድርገው፤ የመምራት ስጦታ ያለው በጥንቃቄ ይፈጽመው፤ምህረት የማድረግ ስጦታ ያለው በደስታ ያድርገው።
ፍቅርን ተከታተሉ ለመንፈሳዊ ስጦታዎችም ከፍተኛ ጉጉት ይኑራችሁ፣
እግዚአብሔርም ምልክቶችን፣ ድንቆችንና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ፣እንደ ፈቃዱ በታደሉት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቱን አጽንቶአል።
ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል
እግዚአብሔር ግን እያንዳንዱን የአካል ክፍል እንደወደደ ሠርቶታል።