ስለ ፍቅር ታላቁ ስጦታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ፍቅር ታላቁ ስጦታ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ነገር ግን እምነት፣ ተስፋ፣ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ግን ጸንተው ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጠው ፍቅር ነው።
በሰዎች እና በመላእክት ልሳኖች ብናገር፣ግን ፍቅር ከሌለኝ፣የሚንጫጫ ቃጭል ወይም የሚጮህ ታንቡር ነኝ።
የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ የተሰወሩ እውነቶችን እና እውቀት ሁሉ ቢኖረኝ፣ተራሮችን ከስፍራቸው የሚያስወግድ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ፣ ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም የማይጠቅም ነኝ።
ፍቅር ፍጻሜ የለውም። ትንቢቶች ያልፋሉ፤ልሳኖችም ቢሆኑ ያበቃሉ፤ዕውቀትም ቢሆን ጊዜ ያልፍበታል።
በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።
ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም።
ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል። ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።
ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ዐዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።»
እርስ በእርስ ከመዋደድ በቀር የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ። ምክንያቱም ባልንጀራውን የሚወድ ህግን ፈጽሟል።
እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡
ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
ፍቅር ያለው ባልንጀራውን አይጎዳም። ስለዚህ ፍቅር የህጉ ፍጻሜ ነው።
አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን።
በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍቅር የሆነ እምነት እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም ትርጉም የለውም።