ስለ መንፈሳዊ ኃይል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መንፈሳዊ ኃይል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2 ጢሞቴዎስ 1:7

እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡

02 ኤፌሶን 3:16

የምጸልየውም ትጠነክሩ ዘንድ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ኀይል እንዲሰጣችሁ ነው።

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ፣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”

04 ኤፌሶን 6:10

በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ የበረታችሁ ሁኑ።

05 ቆላስይስ 1:11

በሁሉም ነገር እንድትጽኑና ትእግሥት እንዲኖራችሁ ፣ከኅይሉ ክብር የተነሣም በሁሉ ብርታትና ጥንካሬ እንዲኖራችሁ እንጸልያለን።

06 1ኛ ቆሮንቶስ 2:4-5

መልእክቴና ስብከቴም የመንፈስን ኃይል በመግለጥ እንጂ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤ ይህም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው።

07 ሮሜ 15:13

በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ ትሞሉ ዘንድ የተስፋ አምላክ በማመናችሁ ምክንያት በደስታና በሰላም ሁሉ ይሙላችሁ።

08 ኤፌሶን 3:20

እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው ሀይሉ መጠን ሁሉንም ነገር እኛ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው

ተዛማጅ ርዕሶች