ስለ ድምጽ ለሌላቸው መናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ድምጽ ለሌላቸው መናገር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 31:8-9

መናገር ለማይችሉ ተናገርላቸው፣ እየጠፉም ላሉት ሁሉ ስለ ጉዳያቸው ተናገር፡፡ ትክክል ስለሆነው ነገር ጮህ ብለህ ተናገር፣ ፍርድም ስጥ፣ ስለ ድሆችና ስለ ተቸገሩም ሰዎች ጉዳይ መልስ ስጥ፡፡

02 ኢሳይያስ 1:17

መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"

ለድኾችና ለሙት ልጆች ተሟገቱ፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ፡፡ ድኾችንና ምስኪኖችን ታደጉ፤ ከዐመፀኞችም እጅ አስጥሏቸው፡፡

04 ኤርሚያስ 22:3

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፣ የተዘረፈውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ። በምድራችሁ ያለውን እንግዳ፣ ወይም የትኛውንም ወላጅ አልባ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። አታምፁባቸው፣ ወይም በዚህ ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።

05 ምሳሌ 24:11-12

ወደ ሞት የሚወሰዱትን አድናቸው፣ እየተጎተቱ ለመታረድ የሚነዱትንም ይዘህ መልሳቸው፡፡ አንተም “እዚያ! ስለዚህ ነገር ምንም አናውቅም” ብትል ልብን የሚመረምረው እርሱ ንግግርህን አያስተውለውምን? ሕይወትህን የሚጠብቀው እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ እንደ ስራው መጠን እግዚአብሔር አይሰጠውምን?

06 ኢዮብ 29:12

ምክንያቱም የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረዳት የሌላቸውን አድን ነበረና።

ለድኾች የሚያስብ ቡሩክ ነው እርሱንም በመከራ ቀን ያህዌ ያድነዋል፡፡

08 አስቴር 4:14

አንቺ በዚህ ጊዜ ዝምታን ብትመርጪ ለአይሁድ እርዳታና መዳን ከሌላ ሥፍራ ይነሣላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ። ወደ ንግሥትነት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ቀን እንደሆነስ ማን ያውቃል?"

09 ምሳሌ 29:7

ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለድሆች ፍትሕ ይጨነቃል፤ ክፉ ሰው ግን እንዲህ ዓይነት እውቀት የለውም፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች