ስለ መታደስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መታደስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 12:2

መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።

02 2ኛ ቆሮንቶስ 4:16

ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም። ምንም እንኳ ውጫዊው ማንነታችን እየደከም ቢመጣም ውስጣዊው ማንነታችን ዕለት በየዕለት ይታደሳል።

03 ኤፌሶን 4:23

በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ

04 ቲቶ 3:5

ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።

05 ኢሳይያስ 40:31

እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።

አምላኬ ሆይ፣ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ

07 ኢሳይያስ 43:19

ተመልከቱ፣ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፣ አታዩትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!

09 ቆላስይስ 3:10

የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።

ወጣትነትሽ እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ ሕይወትሽን በመልካም ነገር ያጠግባል፡፡

11 ኤፌሶን 4:22-24

ክፉ ምኞት የጎደፈውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰው ልታስወግዱ ይገባል። በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።

12 2ኛ ቆሮንቶስ 5:17

ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።

ተዛማጅ ርዕሶች