ስለ ወደ ፊት መገስገስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ወደ ፊት መገስገስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጠርቶ ሽልማቴን ለማግኘት በፊት ወዳለው ግብ እሮጣለሁ።
ወንድሞች ሆይ፤እኔ ራሴ ገና እንደጨበጥኩ አልቆጥርም። ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ይኸውም በስተኋላዬ የነበረውን እየረሰሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እተጋለሉ።
እንደነዚህ ያሉ እጅግ ብዙ ምስክሮች ስላሉን፣ የሚከብደንን ነገር ሁሉና በቀላሉ የሚጠላልፈንን ኃጢአት አሽቀንጥረን እንጣል። ከፊታችን ያለውንም ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ። በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።
በሩጫ ውድድር የሚሳተፉ ሯጮች ሁሉ እንደሚሮጡ፣ ነገር ግን ሽልማት የሚቀበል አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ ሽልማት ለማግኘት ሩጡ።
ኢየሱስ ግን፣ “ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” አለው።
እነዚህን ነገሮች ገና አልጨበጥኩአቸውም ፤ ፍጹም ሆኜአለሁ ማለትም አልችልም። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘሁትን አገኝ ዘንድ ወደ ፊት ጥረቴን እቀጥላለሁ።
መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ እምነቱንም ጠብቄአለሁ፡፡
እንዳትደክሙ ወይም ልባችሁ እንዳይዝል፣ ከኃጢአተኞች የተሰነዘረበትን እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር የታገሠውን እርሱን አስቡ።
በተገቢው ጊዜ ፍሬውን እናጭዳለንና መልካምን ከመስራት አንቦዝን።
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎት እስከምጨርስ ድረስ፣ እንደ ውድ ነገር በመቍጠር፣ ለሕይወቴ አልሳሳላትም።
ስለዚህም ያለ ዓላማ አልሮጥም፣ወይም ንፋስ በቦክስ አልመታም።
ጻድቅ ግን መንገዱን ያጸናል፥ ንጹሕ እጆች ያሉትም ሰው ብርታትን እየጨመረ ይሄዳል።
ጽድቅን የሚያደርግ ሰው መንገድ ግን እየፈካ እንደሚሔድ የንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉ ቀን እስከሚሆን ድረስ ብርሃኑ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
አወጣጡ እንደ ንጋት የታመነ ነው፤ እንደ ካፊያ፥ ምድሪቱን እንደሚያጠጣ እንደ ጸደይ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።