ስለ መንፈሳዊ ዕድገት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መንፈሳዊ ዕድገት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2ኛ ጴጥሮስ 3:18

ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን!

02 1ኛ ጴጥሮስ 2:2

በድነታችሁ በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹህ የሆነውን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤

03 ቆላስይስ 1:10

ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።

04 ኤፌሶን 4:15

ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል።

እርሱም ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ፣ በወራጅ ውሆች እንድ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፡፡

06 ፊልጵስዩስ 1:6

ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።

07 ኤርሚያስ 17:8

በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ተክል ይሆናልና። ሙቀት ሲመጣ አያይም፣ ቅጠሉ ይለመልማልና። ከዚያም፣ በድርቅ ዓመት ላይ አይሠጋም፣ ማፍራቱንም አያቋርጥም።

08 ሆሴዕ 6:3

አወጣጡ እንደ ንጋት የታመነ ነው፤ እንደ ካፊያ፥ ምድሪቱን እንደሚያጠጣ እንደ ጸደይ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።

09 ፊልጵስዩስ 1:9

ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።

10 1 ተሰሎንቄ 3:12

እኛ ደግሞ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ያትረፍርፍም።

ተዛማጅ ርዕሶች