ስለ ከወተት ወደ ጠንካራ ምግብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከወተት ወደ ጠንካራ ምግብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ገና ጠንካራ ምግብ ለመብላት ስላልቻላችሁ ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ጋትኋችሁ። እስከ አሁን ስንኳ ጠንካራ ምግብ ለመብላት ገና አልበቃችሁም።
ወተት ብቻ ሊጋት ማንኛውም ሰው ገና ሕፃን ስለሆነ የጽድቅ ትምህርት ልምምድ የለውም። በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ምግብ ግን መልካምንና ክፉውን መለየት ለተማሩና ትክክል የሆነውን ካልሆነው የመለየት ልምድ ላላቸው ትልልቅ ሰዎች ነው።
በድነታችሁ በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹህ የሆነውን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤
በሰዎች ረቂቅ ተንኮል እና ማታለል በተዘጋጀ የትምህርት ነፋስ ወዲያና ወዲህ የምንነዳ ሕጻናት መሆን አይገባንም
ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣እንደ ልጅ እናገር ነበር፣እንደ ልጅም አስብ ነበር፣የመረዳት ችሎታዬም እንደ ልጅ ነበር። ጎልማሳ ስሆን ግን የልጅነት ነገሮችን አስወገድሁ።
ስለዚህ ስለ ክርስቶስ መልእክት በመጀመሪያ የተረዳነውን ተወት በማድረግ ወደ ብስለት ልንሻገር ይገባናል እንጂ ከሞተ ሥራ ንስሐ መግባትንና በእግዚአብሔር ማመንን፣
ወንድሞች እና እህቶች፣በአስተሳሰባችሁ ልጆች አትሁኑ። ይልቁን ክፋትን በተመለከተ እንደ ሕፃናት ሁኑ። ነገር ግን በአስተሳሰባችሁ ይበልጥ የበሰላችሁ ሁኑ።
ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን!
የምንሰብከው እርሱን ነው። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ለማቅረብ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምክር ሰውን ሁሉ እንገስጻለን።
ስለዚህ እኛ ብዙዎቻችን በመንፈሳዊ ሕይወት እንዳደጉ ሰዎች ነገሮችን ሁሉ ማሳብ ይኖርብናል። ደግሞ በማንኛውም ነገር የተለያየ አስተሳሰብ ቢኖራችሁ እግዚአብሔር ሁሉንም ግልጥ ያደርግላችኋል።
የእውነትን ቃል በትክክል የሚይዝ፣ የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነሀ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ትጋ፡፡
እስከ አሁን ድረስ መምህራን መሆን ሲገባችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ መርሖዎች የሚያስተምራችሁ ሰው ገና ትፈልጋላችሁ። እናንተ የምትፈልጉት ወተት እንጂ፣ ጠንካራ ምግብ አይደለም።