ስለ ከክርስቶስ ጋር መንገሥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከክርስቶስ ጋር መንገሥ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 2 ጢሞቴዎስ 2:12
ብንጸና ከእርሱ ጋር እንነግሣለን፡፡ ብንከዳው እርሱ ደግሞ ይክደናል፡፡
ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
አምላካችንን ያገለግሉ ዘንድ መንግሥትና ካህናት አደረግሃቸው፤እነርሱም በምድር ላይ ይገዛሉ።»
04 ሮሜ 8:17
ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን፥ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከእርሱ ጋር እንድንከብር በርግጥ አብረነው ደግሞ መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ነን።
እኔ ድል እንደነሳሁና በዙፋኑ ላይ ከአባቴ ጋር እንደተቀመጥሁ፥ድል ለሚነሳም በዙፋኔ ላይ ከእኔ ጋር የመቀመጥን መብት እሰጠዋለሁ።
በመጀመሪያው ትንሣኤ ድርሻ የሚኖራቸው ሁሉ የተባረኩና የተቀደሱ ናቸው! እነዚህን በመሳሰሉት ላይ ሁለተኛው ሞት ኅይል አይኖረውም። የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
07 ዳንኤል 7:18
ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፣ ለዘላለምም ይይዙታል።