ስለ ብድራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ብድራት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል። ነገር ግን የማንም ሥራ የተቃጠለበት ከሆነ ይከስራል።
02 የማቴዎስ 6:20
ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት። ከጌታ ዘንድ እንደ ዋጋ የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና።
04 ዕብራዊያን 11:6
ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ፣ እግዚአብሔር እንዳለና እርሱን ለሚሹትም ዋጋን እንደሚሰጥ ማመን ስለሚገባው ነው።
05 የማቴዎስ 16:27
የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክቱ ጋር ይመጣልና፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡
“እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ።