ስለ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እነርሱም፣ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።
ጌታ ራሱ በታላቅ ድምፅ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል፣ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ። ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ነገዶች ሁሉ አምርረው ያለቅሳሉ፡፡ የሰው ልጅንም በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡
“እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ።
ይህም የተባረከውን ተስፋችንን፣ የታላቁን አምላካችንና አዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ፣ ለመቀበል በደስታ እንድንጠባበቅ ነው።
ስለዚህ ጌታችሁ በምን ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተጠንቀቁ፡፡
እነሆ፤እርሱ በደመና ይመጣል፤የወጉትን ጨምሮ ዐይን ሁሉ ያየዋል። የምድርም ነገዶች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤እንደዚያም ይሆናል፤አሜን።
ይሁን እንጂ የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በእሳት ይቃጠላል፤ በምድርና በእርሷም ውስጥ በተሠራው ነገር ሁሉ ላይ ይፈረድበታል።