ስለ የፍርድ ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የፍርድ ቀን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2ኛ ቆሮንቶስ 5:10

እያንዳንዳችን በሰውነታችን በዚህ ምድር ላይ የሰራነውን መልካምም ሆነ ክፉ እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረባችን ግድ ነው።

02 ሮሜ 14:12

ስለዚህም እያንዳንዳችን ስለ ስራችን በእግዚአብሔር ፊት መልስ እንሰጣለን።

03 ዕብራዊያን 9:27

እያንዳንዱ ሰው አንድ ጊዜ መሞት ከዚያ በኃላም ወደ ፍርድ መቅረብ እንደሚገባው ሁሉ

በዙፋኑ ፊት መታን፣ ታላላቆችና ታናናሾች ቆመው አየሁ፤ መጽሕፍትም ተከፈቱ። ከዚያም የሕይወት መጽሐፍ የተባለ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ። መታንም መጻሕፍቱም ውስጥ በተመዘገበው መሠረት እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው

05 የማቴዎስ 12:36

ለእናንተም እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ሰዎች ስለ ተናገሯቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ ይሰጣሉ፡፡

ምክንያቱም በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ የሚፈርድበትን ቀን አዘጋጅቶአል። እግዚአብሔር ይህን ሰው ከሙታን በማስነሣቱ ለሁሉ ሰው ማረጋገጫ ሰጥቶአል።"

07 የማቴዎስ 25:31-32

የሰው ልጅ በክብሩ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ፣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ ሕዝቡን ይለያቸዋል።

ተዛማጅ ርዕሶች