ስለ ቸርነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ቸርነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ኤፌሶን 4:32
በርሳችሁ ቸሮች፥ ርኅሩሆች ሁኑ፤ ደግሞም እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲሁ ይቅር እንዳላችሁ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
02 ቆላስይስ 3:12
ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
03 ገላቲያ 5:22-23
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።
04 ምሳሌ 11:17
ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፣ ጨካኝ ሰው ግን ራሱን ይጎዳል፡፡
05 ሉቃስ 6:35
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ መልካምም አድርጉላቸው፤ ምንም ነገር ስለመቀበል ሳትጨነቁ አበድሯቸው፣ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፡፡ እርሱ ራሱ ለማያመሰግኑና ለክፉ ሰዎች ቸር ነውና፣ እናንተም የልዑል ልጆች ትባላላችሁ፡፡
06 ምሳሌ 19:17
ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ ለሰራውም ቸርነት መልሶ ይከፍለዋል፡፡
ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡