ስለ ፍቅር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ፍቅር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም። ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል። ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።
ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡
ፍቅር ያለው ባልንጀራውን አይጎዳም። ስለዚህ ፍቅር የህጉ ፍጻሜ ነው።
ስለ ወዳጁ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ እንዲሰጥ ግድ ከሚል የሚበልጥ ፍቅር ማንም ሰው የለውም።
አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን።
እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች እያለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያረጋግጣል።
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።
እንደ ወደደን፥ ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።
የማዕበል ውሃ ፍቅርን ለማጥፋት አይችልም፥ ጎርፍም ሊያሰጥመው አይችልም። ሰው በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ብሎ ቢሰጥ ስጦታው ፈጽሞ ይናቃል። የወጣቷ ወንድሞች እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፥
ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።
እግዚአብሔር በኃላፊው ጊዜ ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፣ "እስራኤል ሆይ፣ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ። ስለዚህ በኪዳን ታማኝነት ወደራሴ ሳብሁሽ።