ስለ በተግባር የሚገለጥ ፍቅር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በተግባር የሚገለጥ ፍቅር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ዬሐንስ 3:18

የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣በሥራና በእውነት እንጂ ፣በቃል ወይም በአንደበት አንዋደድ።

02 ያዕቆብ 2:15-16

አንድ ወንድም ወይም እኅት ልብስና የዕለት ምግብ ባይኖራቸው ከእናንተ አንዱ፣ “በሰላም ሂዱ፤ አይብረዳችሁ፤ በደንብ ጥገቡ” ቢላቸው፤ ለአካል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ግን ባትሰጧቸው፣ ምን ይጠቅማል?

03 1ኛ ዬሐንስ 3:17

ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ንብረት ያለውና፣ወንድሙም የሚያስፈልገውን አውቆ፣ባይራራለት፣ እንዴት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ይኖራል?

04 ገላቲያ 5:13

ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።

05 የማቴዎስ 25:40

ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’

06 ያዕቆብ 2:17

ሥራ የሌለው እምነትም እንዲሁ በራሱ የሞተ ነው።

07 1ኛ ዬሐንስ 4:11

ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።

08 ገላቲያ 6:10

ስለዚህም ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ።

09 ዕብራዊያን 13:16

ደግሞም መልካም ማድረግንና እርስ በርስ መረዳዳትን አትርሱ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚደሰተው እንደነዚህ ባሉ መሥዋዕቶች ነው።

10 ሮሜ 12:9

ፍቅራችሁ ያለግብዝነት ይሁን። ክፉ የሆነን ነገር ተጸየፉ፤መልካም የሆነውን ያዙ።

11 ሉቃስ 10:33-34

አንድ ሳምራዊ ግን እየተጓዘ ሳለ ሰውዬው ወደነበረበት መጣ። ባየውም ጊዜ በርኅራኄ ልቡ ተነካ። ወደ እርሱም ጠጋ ብሎ መድኃኒት ካደረገለት በኋላ ቊስሉን በጨርቅ አሰረለት። እርሱ ይጓጓዝበት በነበረበትም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ አመጣው፣ እንክብካቤም አደረገለት።

12 1ኛ ቆሮንቶስ 13:3

ድሆችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ብሰጥ፣ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም አይጠቅመኝም።

ተዛማጅ ርዕሶች