ስለ እርስ በርስ መዋደድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እርስ በርስ መዋደድ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ዐዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።
እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ።
ለእውነት በመታዘዝ ለእውነተኛ የወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልብ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
የርሱም ትዕዛዙ፣በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና፣ ትእዛዙን እንደሰጠን እንደዚያው እርስ በርስ እንድንዋደድ ነው፡፡
እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።»
ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡
ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡
በወንድማማችነት ፍቅር መዋደዳችሁን ቀጥሉ።
የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና።
ከመጀመሪያው የሰማችኋት መልእክት፣ይህ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የሚለው ነው።