ስለ አጥብቆ መያዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አጥብቆ መያዝ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዕብራዊያን 10:23

ተስፋን የሰጠ እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ያለ ማወላወል አጥብቀን እንያዝ።

02 ዕብራዊያን 3:14

ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በእርሱ ያለንን ድፍረት አጥብቀን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች እንሆናለን።

03 1 ተሰሎንቄ 5:21

ሁሉን መርምሩ፣ መልካም የሆነውን ያዙ፣

በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።

05 ፊልጵስዩስ 2:16

ሕይወት የሚገኝበትን ቃል አጥብቃችሁ በምትይዙበት ጊዜ በከንቱ እንዳልሮጥሁና በከንቱም እንዳልደከምሁ ክርስቶስ በሚመለስበት ቀን ለማክበር ምክንያት ሊኖረኝ ይችላል።

ተዛማጅ ርዕሶች