ስለ ጽናት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ጽናት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ቆሮንቶስ 15:58

ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጸናችሁ እና የማትነቃነቁ ሁኑ። ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ሥራ ይብዛላችሁ፣ምክንያቱም በጌታ የምትደክሙት ድካም በከንቱ አይደለም።

02 ያዕቆብ 1:3-4

በፈተና ውስጥ ሳላችሁ በእግዚአብሔር ስታምኑ ይበልጥ ሌሎች ፈተናዎችን በትዕግሥት ለማሳለፍ የሚረዱዋችሁ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡ ክርስቶስን በሁሉም መንገድ ትከተሉ ዘንድ እስከ መጨረሻው በፈተና ጽኑ፤ ያንጊዜ መልካም ማድረግ አይከብዳችሁም፡፡

03 ቆላስይስ 1:23

በእምነት ጸንታችሁ እንድትኖሩ ነው። ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ ተሰብኮአል። እኔም ጳውሎስ አገልጋይ የሆንኩት ለዚህ ወንጌል ነው።

ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስለሆነ አልናወጥም!

05 1ኛ ጴጥሮስ 5:9

በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እንደሚቀበሉ ዐውቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

06 1ኛ ቆሮንቶስ 16:13

ተጠንቀቁ፣በእምነትም ጸንታችሁ ቁሙ፣ቆራጦች ሁኑ፣በርቱ።

07 ያዕቆብ 1:12

በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡

08 ዕብራዊያን 6:19

ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ቅድስት የሚገባውና እኛ የያዝነው ይህ መተማመኛ፣ ሥጋት የሌለበትና አስተማማኝ የነፍሶቻችን መልሕቅ ነው።

09 2ኛ ጴጥሮስ 3:17

እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፤ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ፣ በዐመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ ጽኑ መሠረታችሁን እንዳትለቅቁ ተጠንቀቁ።

እምነቱን ያህዌ ላይ ያደረገ ልበ ሙሉ ስለሆነ ክፉ ወሬ አያሸብረውም፡፡

11 1 ተሰሎንቄ 3:8

በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ እኛ ደግሞ አሁን በሕይወት እንኖራለን።

ተዛማጅ ርዕሶች