ስለ ጽናት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ጽናት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 1:12

በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡

02 ሮሜ 5:3-4

ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን በመከራዎቻችን ደግሞ ደስ ይለናል። መከራ መጽናትን እንደሚያደርግ እናውቃለን። መጽናት ተቀባይነትን፥ ተቀባይነትም ስለ ወደፊቱ መተማመኛን ያስገኛል።

03 ዕብራዊያን 12:1

እንደነዚህ ያሉ እጅግ ብዙ ምስክሮች ስላሉን፣ የሚከብደንን ነገር ሁሉና በቀላሉ የሚጠላልፈንን ኃጢአት አሽቀንጥረን እንጣል። ከፊታችን ያለውንም ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።

04 ገላቲያ 6:9

በተገቢው ጊዜ ፍሬውን እናጭዳለንና መልካምን ከመስራት አንቦዝን።

05 2ኛ ተሰሎንቄ 3:13

እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፣ ትክክል የሆነውን ከማድረግ አትታክቱ፡፡

06 ዕብራዊያን 10:36

ፈቃዱን ካደረጋችሁ በኋላ እግዚአብሔር ለእናንተ ተስፋ የገባውን ነገር ለመቀበል መታገሥ ያስፈልጋችኋል።

07 ሮሜ 8:25

ገና ያላየነውን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ግን እንግዲያው በትዕግስት እንጠባበቀዋለን።

08 ሉቃስ 8:15

ነገር ግን በመልካሙ ዐፈር ላይ የወደቁት በመልካምና በቅን ልብ ካደመጡ በኋላ ቃሉን አጥብቀው የሚይዙ በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።

09 ያዕቆብ 5:11

ልብ በሉ፤ በትዕግሥት የጸኑትን፣ “የተባረኩ” እንላቸዋለን። ስለ ኢዮብ ትዕግሥት ሰምታችኋል፤ ጌታ ለኢዮብ የነበረውንም ዓላማ ታውቃላችሁ፤ ጌታ እጅግ ሩኅሩኅና መሐሪ ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች