ስለ ትዕግሥት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ትዕግሥት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 12:12

ስላላችሁ የወደፊት ተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ትዕግስተኞች ሁኑ፥ጸሎታችሁ የማያቋርጥ ይሁን፤

02 ያዕቆብ 5:7-8

ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ የመጀመሪያውና የኋለኛው ዝናብ እስኪመጣ ድረስ የምድርን ፍሬ በትዕግሥት እንደሚጠብቅ ገበሬ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ ልባችሁን አዘጋጁ፤ ምክንያቱም የጌታ መምጫ ቅርብ ነው።

03 ገላቲያ 5:22

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥

04 ቆላስይስ 1:11

በሁሉም ነገር እንድትጽኑና ትእግሥት እንዲኖራችሁ ፣ከኅይሉ ክብር የተነሣም በሁሉ ብርታትና ጥንካሬ እንዲኖራችሁ እንጸልያለን።

ለምጠብቀው፥ ለምትፈልገውም ሕይወት እግዚአብሔር መልካም ነው። የእግዚአብሔርን ማዳን በዝምታ መጠበቅ መልካም ነው።

06 ኤፌሶን 4:2

ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።

07 ሮሜ 8:25

ገና ያላየነውን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ግን እንግዲያው በትዕግስት እንጠባበቀዋለን።

08 1 ተሰሎንቄ 5:14

ወንድሞች ሆይ እንመክራችኋለን፣ ያለ ሥርዓት የሚመላለሱትን ገስጹአቸው፣ ድፍረት ያጡትን አበረታቱአቸው፣ ደካሞችን ደግፉአቸው፣ሰውን ሁሉ ታገሱ።

09 2 ጢሞቴዎስ 2:24

የጌታ አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፣ ከዚሀ ይልቅ ለሁሉ የሚጠነቀቅ፣ ለማስተማርም የሚበቃ በትእግስትም የሚጸና፣

10 ዕብራዊያን 6:12

ከእምነትና ከትዕግሥት የተነሣ የተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ቸልተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።

ተዛማጅ ርዕሶች