ስለ ከጌታ ጋር ለዘላለም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከጌታ ጋር ለዘላለም የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ጌታ ራሱ በታላቅ ድምፅ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል፣ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ።
አባት ሆይ፣ የሰጠኸኝ እነዚህ ስለ ወደድኸኝ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሰጠኸኝን ክብር እንዲያዩ እኔ ባለሁበት እነርሱም ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እወዳለሁ፡፡
ከዙፋኑም እንዲህ የሚል ታላዝ ድምፅ ሰማሁ፣ “እነሆ የእግዚአብሔር መኖሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱ ጋር ይኖራል። እነርሱ ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ራሱም ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል።
በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ዘወትር ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤ በያህዌም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ፡፡
ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ ዳግመኛ እመጣለሁ፣ ወደ ራሴም እወስዳችኋለሁ።`
ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል፡፡ በምክርህ ትመራኛለህ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ፡፡
ስለዚህ ይህ ድፍረት አለን፤ከሰውነታችን ተለይተን ከጌታ ጋር በሰማይ ቤት መሆንን እንመርጣለን።
ምክንያቱም በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተወጥሬአለሁ። በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ።
ዓለሙና ምኞቱም ያልፋሉ፣የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡