ስለ እምነት ከመስማት ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ እምነት ከመስማት ነው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 10:17

ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ሲሆን መሰማት ያለበትም የክርስቶስ ቃል ነው።

02 ዮሐንስ 20:31

ነገር ግን ይህ የተጻፈው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑና አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንድታገኙ ነው።

03 ገላቲያ 3:2

ይህን ብቻ ከእናንተ ማወቅ እፈልጋለሁ። መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት በህግ ሥራ ነው ወይስ የሰማችሁትን በማመናችሁ?

04 1ኛ ጴጥሮስ 1:23

ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ ነገር ግን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው።

05 ሮሜ 10:14

ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ስለእርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል?

06 ሮሜ 10:8

ነገር ግን ቃሉ ምን ይላል? «ቃሉ ለአፍህና ለልብህ ቅርብ ነው።» ይላል። የምንሰብከው የእምነት ቃል ይህ ነው።

07 ዮሐንስ 17:20

ከእነርሱ ምስክርነት የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑት ሁሉ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልጸልይም፡፡

ነገር ግን መልእክቱን ከሰሙት ብዙ ሰዎች አመኑ፤ ያመኑት ሰዎች ቍጥርም ዐምስት ሺሕ ያህል ነበረ።

ተዛማጅ ርዕሶች