ስለ የታመነ ሆኖ መቆጠር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የታመነ ሆኖ መቆጠር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በዚህ መሠረት መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይገባቸዋል።
ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።
ለዚህ አገልገሎት ታማኝ እንድሆን ያበቃኝንና የሾመኝን፣ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ፡፡
በጥቂቱ የታመነ ሰው በብዙ ላይ የታመነ ይሆናል፤ በጥቂቱ የሚያምፅ በብዙም ዐመፀኛ ይሆናል።
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ። ተመልከት ከእናንተ አንዳንዶቹን እንድትፈተኑ ዲያብሎስ እስር ቤት ያስገባችኋል፤ ለአሥር ቀን መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
ከብዙ ምስክሮች ጋር ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡
ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።' አለው።
የተወደድክ ሆይ ለወንድሞችም ሆነ ለእንግዶች በምታድርገው ነገር ስላለህ ታማኝነት
ታማኝ ሰው ታላቅ በረከት ያገኛል፣ በጥድፊያ ሃብታም የሆነ ግን ሳይቀጣ አይቀርም፡፡
እንግዲህ ማንም ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የተሰወረው ምሥጢር መጋቢዎች እንደሆነን ሊቆጥረን ይገባል።
አገልጋዬ ሙሴ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እርሱ በቤቴ ላይ ሁሉ የታመነ ነው፡፡
ወደ ፊት መነገር ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን፣ ሙሴም በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር።
በዚህ ምክንያት የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ ዳንኤል በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ እንከን ለማግኘት ፈለጉ፤ ነገር ግን ዳንኤል ታማኝ ጠንቃቃና በሥራው እንከን የሌለበት ስለነበር በእርሱ ላይ ስህተት ሊያገኙ አልቻሉም።