ስለ በቃሉ መጽናት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በቃሉ መጽናት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ኢየሱስ በእርሱ ያመኑትን አይሁድ፣ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ፣ በርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።
በእኔ ብትኖሩ፣ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ ይሰጣችኋል።
በእምነት ጸንታችሁ እንድትኖሩ ነው። ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ ተሰብኮአል። እኔም ጳውሎስ አገልጋይ የሆንኩት ለዚህ ወንጌል ነው።
ፍጹሙንና ነጻ የሚያወጣውን ሕግ በጥንቃቄ የሚመለከትና የሚኖርበት እንጂ፣ ሰምቶ እንደሚረሳው ያልሆነ ሰው በሚያደርገው ሁሉ የተባረከ ይሆናል።
በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ካልኖረ በቀር በራሱ ፍሬ ማፍራት እንደማይችል ሁሉ፣ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
እናንተ ግን ፣ከመጀመሪያው የሰማችሁት በውስጣችሁ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት፣በእናንተ ቢኖር፣እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤በመዝሙርና በውዳሴ፤ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
አንተ ግን በተማርህበትና በምታምንበት ነገር ጸንተህ ኑር፣ ከማን እንደተማርከው ታውቃለህና፡፡
ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በእርሱ ያለንን ድፍረት አጥብቀን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች እንሆናለን።
እነርሱም ሐዋርያት በሚያስተምሩት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውን በመቊረስና በጸሎትም ይተጉ ነበር።
ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «ማንም ሰው ቢወደኝ ቃሌን ይጠብቃል። አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱ እንመጣለን፣ መኖሪያችንንም በእርሱ እናደርጋለን።
ሥራህን ዐውቃለሁ፤እነሆ፤ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ዐቅምህ ትንሽ እንደሆነ አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ስሜንም አልካድህም።