ስለ ቃልን በልብ መደበቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ቃልን በልብ መደበቅ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ፡፡

እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤ በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው።

03 ቆላስይስ 3:16

የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤በመዝሙርና በውዳሴ፤ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።

ጐልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው፡፡

05 ምሳሌ 7:1-3

ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ጠብቅ፣ ትእዛዜንም በአንተ ውስጥ አኑር፡፡ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፣ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፡፡ በጣቶችህም ላይ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ጻፋቸው፡፡

ስለዚህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደ ክታብ ይሁኑላችሁ። ፥

ተዛማጅ ርዕሶች