ስለ ቃሉ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ቃሉ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኢሳይያስ 40:8

ሣሩ ይደርቃል፣ አበባውም ይረግፋል፣ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።"

02 1ኛ ጴጥሮስ 1:24-25

ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። የተሰበከላችሁም ወንጌል መልእክቱ ይህ ነው።

03 የማቴዎስ 24:35

ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም፡፡

ያህዌ ሆይ፣ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡

05 ማርቆስ 13:31

ሰማይና ምድር ያልፋል፣ ቃሌ ግን አያልፍም፡፡

ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው ጥንት ከሥርዐትህ ተምሬአለሁ፡፡ ሬስ

07 ሉቃስ 21:33

ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።

ያህዌ ቸር ነው፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነው፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው፡፡

09 ኢሳይያስ 59:21

ከእርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፣ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፣" ይላል እግዚአብሔር።

የያህዌ ቃሎች የነጹ ቃሎች ናቸው በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው፡፡ ያህዌ ሆይ፣ አንተ ትጠብቀናለህ ከዚህ ዐመፀኛ ትውልድ ለዘላለም ጻድቃንን ትጠብቃለህ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች