ስለ ቃልን ማሰላሰል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ቃልን ማሰላሰል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኢያሱ 1:8

ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ።

ነገር ግን ደስ የሚሰኘው በያህዌ ሕግ ነው ሕጉንም ቀንና ሌሊት ያሰላስላል፡፡ እርሱም ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ፣ በወራጅ ውሆች እንድ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፡፡

ድንጋጌህን አሰላስላለሁ መንገድህም ላይ አተኩራለሁ፡፡

አቤቱ ሕግህን ምንኛ ወደዱሁ ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ፡፡

05 ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።

ቃልህን አሰላስል ዘንድ ሌሊቱን ሙሉ ዐይኔ ሳይከደን ያድራል፡፡

በመኝታዬ ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ፡፡

የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ አንተ ያደረግኸውንም አውጠነጠንሁ፡፡

ሥራዎችህን ሁሉ አሰላሰላለሁ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች