ስለ ግራ መጋባት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ግራ መጋባት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ ግራ የመጋባት አምላክ አይደለም። በሁሉም የአማኞች አብያተክርስቲያናት ውስጥ፦
ምክንያቱም ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ባለበት ሁከትና ክፉ ሥራ ይኖራል።
ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡
በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበት መንገድ እመራሃለሁ እመክርሃለሁ ዐይኔንም አንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ ራሴ አውቃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የጥፋት አይደለም።
ልባቸው ተጽናንቶና በፍቅር ተሳሰረው ፍጹም የሆነ የመረዳት ብልጽግና እንዲኖራቸውና የእግዚአብሔርን ምስጢር የሆነውን እውነት ክርስቶስን እንዲያውቁ እታገላለሁ። የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።