ስለ አሳብን በላይ ማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ አሳብን በላይ ማድረግ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ቆላስይስ 3:2
በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
02 ቆላስይስ 3:1
እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ።
03 የማቴዎስ 6:33
ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
04 ፊልጵስዩስ 3:20
ነገር ግን የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠብቅ የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን።
05 ሮሜ 8:5-6
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ስለሥጋዊ ነገሮች ያስባሉ፥እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን ስለመንፈስ ቅዱስ ነገሮች ያስባሉ። የሥጋ አስተሳሰብ ሞት ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ አስተሳሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
የሚታዩትን ነገሮች ሳይሆን የማይታዩትን ነገሮች እንመለከታለን። የምናያቸው ነገሮች ጊዜያዊ ሲሆኑ የማይታዩት ነገሮች ግን ዘላለማዊ ናቸው።
07 ዕብራዊያን 12:2
በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።
08 የማቴዎስ 6:21
ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡
09 ዕብራዊያን 11:16
አሁን ግን የሚፈልጉት የተሻለውን ሰማያዊ አገር ነው። ስለዚህም፣ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አያፍርም።