ስለ አእምሮን ማደስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አእምሮን ማደስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 12:2

መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።

02 ኤፌሶን 4:23

በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ

03 ቆላስይስ 3:10

የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።

04 ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።

05 2ኛ ቆሮንቶስ 5:17

ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።

06 ቲቶ 3:5

ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።

07 ኤፌሶን 4:22-24

ክፉ ምኞት የጎደፈውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰው ልታስወግዱ ይገባል። በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።

08 1ኛ ጴጥሮስ 1:13

ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጠቁ፤ ጠንቃቆች ሁኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በምታገኙት ጸጋ ላይ ፍጹም መተማመን ይኑራችሁ።

ተዛማጅ ርዕሶች