ስለ ትሕትናን መልበስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ትሕትናን መልበስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 1ኛ ጴጥሮስ 5:5
ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ ምክንያቱም፣ «እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንደ ተባለው፣
02 ቆላስይስ 3:12
ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
03 1ኛ ጴጥሮስ 5:6
እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤
04 ፊልጵስዩስ 2:3
በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።
05 ምሳሌ 11:2
ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፣ ከትህትና ጋር ግን ጥበብ ትመጣለች፡፡
06 ያዕቆብ 4:6
እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው።