ስለ አባ አባት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ አባ አባት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ተመልሳችሁ እንድትፈሩ የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም። ይልቅ የተቀበላችሁት "አባ፥አባት" ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ነው።
ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።
አባት ሆይ ለአንተ ሁሉ ይቻላል ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን አለ፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
እንግዲህ እንደዚህ ጸልዩ፡- ‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፡
ኢየሱስም«ገና ወደ አብ አልሄድሁምና አትንኪኝ፣ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ መሄዴ ነው ብለሽ ንገሪአቸው» አላት።
በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ።
በኢየሱስ አማካይነት እኛ ሁለታችንም በአንድ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።
ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡
ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።